እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100): በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጉዋቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጉዋል::
+መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ:-
1.አጋእዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አህን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው)
2.ኪሩቤል (አለቃቸው ኪሩብ)
3.ሱራፌል (አለቃቸው ሱራፊ)
4.ኃይላት (አለቃቸው ሚካኤል)
5.አርባብ (አለቃቸው ገብርኤል)
6.መናብርት (አለቃቸው ሩፋኤል)
7.ስልጣናት (አለቃቸው ሱርያል)
8.መኩዋንንት (አለቃቸው ሰዳካኤል)
9.ሊቃናት (አለቃቸው ሰላታኤል)
10.መላእክት (አለቃቸው አናንኤል) ናቸው::
+ከእነዚህም
*አጋእዝት:
*ኪሩቤል
*ሱራፌልና
*ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው::
*አርባብ:
*መናብርትና
*ስልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው::
*መኩዋንንት:
*ሊቃናትና
*መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው::
+መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::
+ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::
ቅዱሳን መላእክተ ብርሃን: መንፈሳውያን: ሰባሕያን: መዘምራን: መተንብላን (አማላጆች) ተብለውም ይጠራሉና ያስቡን ዘንድ ልናስባቸው ይገባል::
የመላእክት ባሕርይ እንዴት ነው?
የመላእክት ባሕርይ ከሰው ጋር የሚያመሳስለውም የሚያለያየውም ነጥብ አለው፡፡ ከሰው በምን ይለያሉ ቢሉ መላእክት፡-
· ረቂቃን ናቸው፡፡ ከነፋስ ነፍስ ትረቃለች፤ ከነፍስ መላእክት ይረቃሉ፤ ከመላእክት ደግሞ ሥላሴ ይረቃሉ፡፡
· እንደ ሰው አይራቡም፤ አይጠሙም፡፡ ልብስ፣ መጠለያ አይፈልጉም፡፡ “እኔም ተገለጥኩላችኁ፤ ነገር ግን እይታን አያችኁ እንጂ ከእናንተ ጋር አልበላኹም፤ አልጠጣኹምም” /ጦቢት 12፡19/፡፡
· የመላዕክት ምግባቸው የእግዚአብሔር ምስጋና መጠጣቸውም የመለኮት ፍቅር ነው፡፡
· መላዕክት ፆታ የላቸውም /ማቴ.22፡30-31/፡፡ በመኾኑም አይጋቡም፤ አይዋለዱም፡፡
· ስለ ነገ አይጨነቁም፡፡
· መላዕክት ከዝንጋዔ የራቁ፣ ባለ አዕምሮ የኾኑ፣ ዕውቀት ያላቸው፣ ይዋኄንና ትዕግሥትን ገንዘብ ያደረጉ፣ ለዘለዓለም የማይነጥፍና የማያቋርጥ ይልቁንም ዘወትር እንደ ዥረት ውኃ የሚወርድ ምስጋና ያላቸው ናቸው /ሥነ ፍጥረት፣ በቀሲስ ስንታየኁና በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ የተዘጋጀ፣ ገጽ 34/፡፡
· ምንም እንኳን ከሰው በፊት ቢፈጠሩም አያረጁም፡፡ ዘወትር ውቦች፣ ብርቱዎችና ውርዙዋን ናቸው፡፡
· ኢ-መዋትያን ናቸው (አይሞቱም) /ሉቃ.20፡36/፡፡ ይኸውም ልክ እንደ እኛ ነፍስ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተደረገ ነው፡፡
· እንደ ሰው አንድ ጊዜ ደግ ሌላ ጊዜ ክፉ በመሥራት አይዋልሉም፡፡
ከሰው ምን ያመሳስላቸዋል ስንል ደግሞ፡- ምንም ረቂቃን ቢኾኑም ሕልውና ከአካል ጋር አላቸው፡፡ ዮሐንስ ዘደማስቆ የተባለ አባት ይኽን ሲያብራራው፡- “መላእክት ረቂቃን ናቸው የምንላቸው ከእኛ አንጻር ነው፡፡ ከማንም ጋር ከማይነጻተረው ከእግዚአብሔር አንጻር ሲታዩ ግን ግዙፋን ናቸው፡፡ ፍጹም ረቂቅ እግዚአብሔር ብቻ ነውና” ብሏል፡፡
ምንም ረቂቃን ቢኾኑም ውሱናን ናቸው፡፡ እንደ ሰው በቦታ የሚገቱ ባይኾኑም መጠን አላቸው፡፡ መጠናቸውና አርዐያቸውም የተለያየ ነው፡፡ ቁመታቸው ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ መላዕክት አሉ፡፡ በክንፋቸው ብቻ አንድ አገር የሚያለብሱ መላዕክት አሉ፡፡ ራሳቸው ብቻ ተራራ የሚያክሉ መላዕክት አሉ፡፡ በዓይን የተቀረፁ የተሸለሙ ኹለንተናቸው ዓይን የኾነ መላዕክት አሉ፡፡ ስድስት ክንፍ ያላቸው መላዕክት አሉ፡፡ መብረቅ ለብሰው መብረቅ ተጐናጽፈው የሚኖሩ መላዕክት አሉ፡፡ ነፋስ ለብሰው ነፋስ ተጐናጽፈው የሚኖሩ መላዕክት አሉ፡፡ ብሩህ ደመና ጠምጥመው የሚኖሩ መላዕክት አሉ፡፡ እግራቸው ዓምደ እሳት የሚመስል መላዕክት አሉ፡፡ የእነዚኽን መላዕክት አርዓያቸውን መጠናቸውን ከእግዚአብሔር በቀር የሚያውቀው የለም /ኩፋ.2፡7-8/፡፡

ዐዋቂዎች ናቸው
ዕውቀታቸው ግን ሐዋርያው ጴጥሮስ እንደተናገረው ከሰው እጅግ ከፍ ያለ ነው /2ኛ ጴጥ.2፡11/፡፡ ምንም ከሰው እጅግ ከፍ ያለ ቢኾንም ግን ዕውቀታቸው መጠን አለው፡፡ ከእግዚአብሔርን በቀር ፍጹም ዕውቀት ያለው የለምና፡፡ እኛ ዕውቀታችን እንደ መላእክት የሚኾነው ከትንሣኤ ዘጕባኤ በኋላ ነው /1ኛ ቆሮ.13፡12/፡፡
ነጻ ፈቃድ አላቸው
እንደ ሰው ባሕርያቸውን የሚገልጽ ስም አላቸው፡፡
ሰው ከመበደሉ በፊት ልክ እንደ መላእክት ንጹሕ፣ ውብና ብርቱ ነበር፡፡ በፍጥረታት ላይ ሥልጣን ነበረው፡፡ ርሱ ሲበድል ግን ከሥልጣን የወረደ ሰው እንደ ድሮ የሚያከብረው እንደሌለ ኹሉ ፍጥረታቱ አዳምን አልታዘዝ አሉት፡፡ እንደዉም ተበረታቱበት፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣውም ወደ ቀድሞ ክብራችን ወደ ልጅነት ወደ ቀድሞ ቦታችን ወደ ገነት ከዚያም በላይ ወደ መንግሥተ ሰማያት ሊመልሰን ነው፡፡ በመኾኑም ሰው ምንም እንኳን በዚኽ ዓለም ሳለ ብዙ ውጣ ውረዶችን ቢያሳልፍም በመጨረሻ መላእክትን ይመስላል፡፡ ለዚኽም ነው ቅዱሳን መላእክት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ.1፡14 ላይ እንደገለጸው ታናሽ ወንድማቸውን ሰውን በማገልገል ላይ ያሉት፡፡

<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>
.jpg)

No comments:
Post a Comment