ሃይማኖት2


 አምስቱ አዕማደ ምስጢራት

ምስጢረ ሥላሴ
ምስጢረ ሥጋዌ
ምሥጢረ ጥምቀት
ምስጢረ ቁርባን
ምስጢረ ትንሳኤ ሙታን  

     ‹‹
አምድ›› ማለት ‹‹ምሶሶ›› ማለት ሲሆን ‹‹አዕማድ››ማለት ደግሞ ምሶሶዎች ማለት ነው፡፡
አዕማደ ምስጢር ማለት ደግሞ ‹‹የምስጢር ምሶሶዎች ማለት›› ነው፡፡
እነዚህ ምስጢራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሠረታዊ የሆኑ የሃይማኖት አስተምህሮዎች
የሚገለጡባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ምስጢር ለምን ተባሉ ስንል በጣም ረቂቅና የሰው ልጆች ሕሊና መርምሮ ሙሉ ለሙሉ ለመረዳት ከባድ ስለሆኑነው፡፡ እነዚህ ምስጢራት ለክርስቲኖች ብቻ የሚነገሩ በመሆናቸው ነው፡፡ 

የአዕማደ ምስጢር ምንጭና ስያሜ መሰረቱ ምንድን ነው?

አዕማደ ምስጢራት ይዘት ምንጭ የጌታና የሐዋርያት ትምህርት ነው፡፡
ይሁን እንጅ አነሳሱ በጸሎተ ሃይማኖት ወይም አባቶቻችን ምዕመናንን በትክክለኛው ሃይማኖት ለማጽናትና መናፍቃንን ድል ለመንሳት በተካሄዱ በጉባዔ ኒቂያና ቁስጥንጥንያ ነው፡፡
ከዚህ በኋላ አባቶቻችን ጸሎተ ሃይማኖትን መሰረት በማድረግ ከብሉያት ከሐዲሳትና ከሊቃውንት መጽሃፍት በማውጣጣት አምስቱ አዕማደ ምሥጢራትን አዘጋጅተዋል፡፡



 . ምስጢረ ሥላሴ

‹‹ሥላሴ››የሚለው ቃል ‹‹ሠለሰ ሦስት አደረገ ›› 
ካለው የግዕዝ ግዝ የተገኘ ሲሆን ሦስትነት ማለት 
ነው፡፡
ይህ ምስጢር የእግዚአብሔርን አንድነት ሦስትነት 
የምንማርበት የትምህርት ክፍል ነው፡፡ይህም ልዩ ሦስትነት ይባላል፡፡
ይህም እግዚአብሔር አንድ አምላክ በሦሰት አካል/ኩነታት ወይም ሁኔታዎች/ለአበው፣ ለነቢያት
 ለሐዋርያት የተገለጠውን መሰረትበማደረግ ነው፡፡
በአጭር ቃል በባህርይ፣በፈቃድና በስልጣን አንድ 
የሆነውን እግዚአብሔር፣የአካል፣የስምና የግብር
ሦስትነት እንዳለው የምናምነው እምነት 
ምሥጢር ሥላሴ ይባላል፡፡

የቤተክርስቲያን አርማ


   ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተክርስቲያን አርማ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ በአሉት 
 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልግሎት ላይ እንዲውል ወ ሰነ ።ከዚህ በፊት ይህ አርማ በቅዱስ ሲኖዶስ ቅጥር ግቢ ብቻ አገልግሎት ይሰጥ ነበር።
ይህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አርማ እንጂ ሰንደቅ ዓላማ አይደለም፡፡ ሰንደቅ ዓላማን በተመለከተ የሚወሰነው በፓርላማ ወይም በሕዝበ ውሳኔ ነው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ባንዲራ ወይም ሰንደቅ ዓላማ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያን አርማ ነው ያወጣችው እርሱም በ፳፻፯ዓ.ም. በወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ፬ ላይ በግልጽ ተደንግጓል፡፡
አንቀጽ ፬ የቤተ ክርስቲያን ዓርማ፤
፩.የዓርማው ቅርጽና ይዘት፤
፩፥፩.መደቡ ነጭ፡፡
፩፥፪.ዙሪያው የስንዴ ዛላና የወይን ዘለላ፡፡
፩፥፫.ከላይ ከአናቱ አክሊል፤ ከታች ከግርጌው መሐል ለመሐል ወጥቶ አናቱ ከአክሊሉ ሥር የደረሰና መስቀል ያለበት አርዌ ብርት፡፡
፩፥፬.በግራ ኹኖ በቀኝ እጁ አርዌ ብርት፤ በግራ እጁ ዘንባባ የያዘ መልአክ፤ በቀኝ ኹኖ በግራ እጁ አርዌ ብርት በቀኝ እጁ ዘንባባ የያዘ መልአክ፡፡
፩፣፭.ከአርዌ ብርቱ ሥር «ነዋ ወንጌለ መንግሥት» ተብሎ የተጻፈበት ቅዱስ መጽሐፍ፡፡
፩፥፮.ከቅዱስ መጽሐፍ ሥር መስቀለኛ የ «ጸ» ፊደል ቅርፅን የሚመስል፤ ኹለቱ ጫፎቹ ከመደቡ ወደ ውጭ የወጣ ሰበን፡፡
፩፥፯.የስንዴ ዛላና የወይን ዘለላ በተገናኙበት የዓለም ምስል፤ ያለበት ይኾናል፡፡

ሃይማኖት 1


ሃይማኖት ሃይመነ አሳመነ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በአንድ አምላክ ማመን እና ለአንድ አምላክ መታመን ማለትን ያመለክታል ::

  በዓይናችን ለምናየው ለግዙፉ ዓለምና ለማይታየው ለረቂቁ ዓለም ፈጠሪ አስገኝ መጋቢአለው እሱም እግዚአብሔር ነው ብሎ ማመን የሃይማኖት የመጀመሪያ ክፍል ነው

    እምነት ማለትም አምነ አመ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሆኖ ትርጉሙ ለእግዚአብሔር መታመንነና በእግዚአብሔር ማመንን ይገልጣ ነው ቅዱስ ዻውሎስዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደተፈጠሩ የሚታየውም ከማይታየው እንደሆነ እናውቃለንዕብ 11 3  በማለት እንደተናገረ የሰው ልጅ የሃይማኖት ትምሕርት ከመማሩ አስቀድሞ በህሊናው በመመራት የእግዚአብሔርን መኖር ማመን ተገቢ ነው

  የሃይማኖት ትምሕርት የሚነገረው የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን በመቀበል የምናምነው የምንማርበት እንጅ እንደ ዓለማዊ የሳይንስ ዕውቀት የተማርነው ሁሉ በዘመናዊ መሳሪያ አረጋግጠን የምንደርስበት አይደለም ሃይማኖት ቁስ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ታምነው የሚኖሩት ሕይወት ነውና የእግዚአብሔር መንግሥት ተቃዋሚዎች አጋንንት ሳይቀሩ አይጠቀሙበትም እንጅ የአምላክን መኖር ያምናሉ ይንቀጠቀጣሉም ያዕ 2 19

    በዚህ ዓለም በራሱ የተገኘ ምንምነገር እንደሌለና ለሁሉም አስገኝ ፈጣሪ እንዳለው ይታወቃል የሳይንሱ የምርምር ውጤት፡ ሁሉን የፈጠረው ኃይል በሥጋዊ ጥበብ ተመራምሮ አልደረሰበትም በሃይማኖት ትምሕርት ግን ሁሉን ያስገኘ እግዚአብሔ መሆኑን መረዳት ይቻላል የሰው ልጅ የሠራቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚያንቀሳቅስ ባለሞያ እንደሚያስፈልጋቸው ሁሉ ይህን ዓለምም የሚያንቀሳቅሰውና የሚመራው አስገኝው (የፈጠረው) አምላክ ብቻ ነውና ሰው ይህን የአምላክ ሥራ አይቶ ፈጣሪውን ማመስገን ሲገባውየተፈጥሮ ክስተት ነውሲል ይደመጣል

አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ

    የከበረ ገድለኛ አባት የዋልድባው አባ ሳሙኤል የአባቱ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም ደግሞ ዓመተ ማርያም ነው። እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጋግ ናቸው፤ እነርሱም በአክሱም ሀገር ሲኖሩ ሁለት ልጆችን ወለዱ። አንደኛው ስሙ...

በብዙ አንባቢያን የተነበቡ