ልደተ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ


ልደተ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፦ (በምሥጢረ ሥጋዌ አስተምህሮ)

   
ክፍል አንድ
               
       
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
      ተሠገወ፡- ማለት ሰው ሆነ ማለት ነው። ስለዚህሥጋዌሰው መሆንን፣ መገለጽን (በተአቅቦ) መግዘፍን፣ መወሰንን፣ መዳሰስን ያመለክታል። ቀድሞ ምን ነበር? ወይም ማን? ለሚለው ጥያቄ በቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልበመጀመሪያ ቃል ነበረ። ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረተብሎ ተገልጿል። (ዮሐ.11) ሰው የሆነም አካላዊ ቃል እንደሆነቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ።በማለት አስረግጦ ተናግሯል። (ዮሐ.114) ሰው የሆነውም በተዋሕዶ ነው። ይኸውምአንድ ጊዜ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነውበማለት ነው። ምሥጢረ ሥጋዌ የአብ አካላዊ ቃል ወልድ ሰውን ለማዳን ሲል ሰው የሆነበት፤ ሰውንም ያዳነበት መለኮትና ትስብእት በተዋሕዶ አንድ የሆኑበት ምሥጢር ማለት ነው።
      ከተዋሕዶ በኋላ ምንታዌ (ሁለትነት) የለም። ሞትን በቀመሰ ጊዜም መለኮት ከሥጋም ከነፍስም አልተለየም። በዚህም ምክንያት ሞቱ እንደሌሎች ፍጡራን ወይም እንደ ሌሎች ሰዎች ሞት የማይታይ መሆኑን ቅዱስ ጳውሎስእርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፤ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው።ሲል ገልጦልናል። (ዕብ. 214) በመሆኑም ሲራብም፣ ሲበላም፣ ሲጠጣም፣ ሲተኛም፣ ሲነሳም፣ ተዓምራት ሲያደርግም፤ በአንድ ባሕርይ ጸንቶ እንጂ እንደ ማየ ግብጽ በሚጠት አንድ ጊዜ አምላክ አንድ ጊዜ ሰው እየሆነ አይደለም።

የንስሃ መንገዶች


የንስሃ መንገዶች (በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

አምስት የንስሃ መንገዶች አሉ ። የተለያዩ ቢሆኑም ቅሉ ሁሉም የሚያደርሱት ግን ርስት መንግስተ ሰማያት ነው ። እነርሱስ ምን ምን ናቸው ? ያልከኝ እንደሆነ እንድህ ብየ እመልስልሃለሁ፦

፩ኛ • የመጀመሪያው መንገድ "የራስን ኃጢአት ማመን፣ መጥላትና ማውገዝ ነው።

ይኽውም ልዑል ቃል ኢሳይያስ "እንድትጸድቅ መጀመሪያ ኃጢአትህን ተናገር እንዳለው" (ኢሳ 43 ፥26 )፤ ክቡር ዳዊትም "በደሌን አልሸፈንኩም፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እንግራለሁ አልሁ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውኽልኝ" ብሎ እንደተናገረ (መዝ 31፥5) ስለዚህ አንተም ስለ ሰራኽው ኃጢአት እራስህን ውቀሰው። በዚህ እግዚአብሔር ይቅር እንዲልህ ታደርገዋለህና። ይህ ብቻ ሳይሆን ስለ ኃጢአቱ እራሱን የሚወቅስና ኃጢአቱን የሚኮንን ሰው በተመሳሳይ ኃጢአት በቀላሉ አይወድቅምና። ስለዚህ በጌታ የፍርድ ዙፋን የሚወቅስህ እንዳይኖር ዛሬ እውነተኛ ወቃሽ በኾነው ሕሊናህን አንቅተህ በራስህ ላይ ወቃሽና ከሳሽ አድርገህ ሹመው። ይህ አንዱና ደገኛው መንገድ ነው ።

፪• ሁለተኛው የንስሐ መንገድ ደግሞ የወገኖቻችንን በደል ይቅር ማለትና በበደሉህ ላይ ቅሬታና ቂም አለመያዝ ነው።

ክፍል ሦስት ‹‹ተዋሥኦተ ቀሲስ አባ ጳውሊ›› (የመጨረሻው ክፍል)



ክፍል ሦስት
‹‹ተዋሥኦተ ቀሲስ አባ ጳውሊ›› (የመጨረሻው ክፍል)
‹‹ዳግመኛም ሕዝቡን፣ ቀሳውስቱን፣ ካህናቱን፣ ሊቃውንቱን እንዲነቅፉ አደርጋለሁ፡፡ ሁላቸውንም ከጽድቅ ሥራ ሰንፈው ለኃጢአት ሥራ እንዲተጉ አደርጋቸዋለሁ፡፡ ንስሓ እንዳይገቡ በውስጣቸው ፍርሃትን፣ ትምክህትን፣ ስንፍናን አሳድርባቸዋለሁ፡፡ በዚህ ምክንያት የወንድሞቻቸውን
ኃጢአት እንጂ የራሳቸውን ኃጢአት አይናዘዙም፡፡ በዚህም ምክንያት ለበደላቸው ሥርየት የላቸውም፡፡ ከኃጢአት እንዳይርቁ በእነርሱ ላይ የማላመጣው ምክንያት የለም፡፡ ምክሬን ከሰሙኝ ፈጽሜ የክርስቶስን ጸጋ አሳጣቸዋለሁ›› አለው፡፡ አባ ጳውሊም ይህን ሰምቶ ፈጽሞ አለቀሰ፡፡ ሰይጣንም አባ ጳውሊ ሲያለቅስ ባየ ጊዜ ደስ አለው፡፡ ይስቅበትም ጀመር፡፡ ‹‹እንደ አንተ ካህናት ናቸውና ስለእነርሱ ታለቅሳለህን?›› አለው፡፡ ‹‹በእውነት ማልቀስ ከወደድክ ስለሊቃውንት፣ ስለደጋግ ነገሥታትና ሥልጣናት፣ ስለመኳንንት፣ ስለገዥዎች መታጣት ፊትህን ጸፍተህ አልቅስ፡፡ ዳግመኛም ስለንጹሐን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ስለኤጲስቆጶሳት፣ ስለቆሞሳትና ስለደጋግ ንጹሐን ካህናት መታጣት አልቅስ፡፡ አብዝተህ ስለቤተ ክርስቲያን በገዳም ስለሚኖሩና ስለገዳማትም አልቅስ፡፡ ይልቁንም ስለወንድሞችህ መነኮሳትን ስለእኅቶችህ መነኮሳይያት ፈጽመህ አልቅስ በኋላ ዘመን ዘመዶቼና ወዳጆቼ አደርጋቸዋለሁና›› አለው፡፡ አባ ጳውሊም ፈጽሞ እያዘነ ‹‹በምን ሥራ እንዲህ ታደርጋቸዋለህ?›› አለው፡፡ ሰይጣንም ‹‹እነርሱ ራሳቸው በፈቃዳቸው ጎዳናዬን ሁሉ ይከተላሉ፣ ፈቃዴንም ይሠራሉ፡፡ የማሳስባቸውንም ይሠራሉ፣ ቃሌንም አይተላለፉም›› አለው፡፡

ኅዳር 21



ኅዳር 21 የሚከበረውን የእመቤታችን በዓል በማድረግ ስለ ታቦተ ጽዮን አሰራርና ምሳሌነት እንዲሁም ስለ ታቦትና ከሀዲዎች ከሁለት መጻህፍት ምንጭ በማድረግ ቃል በቃል የሰፈረ
በዲ/ አውራሪስ በላይ
‟"እኛን ክርስቲያኖች መስለው የገቡ አባታቸው ዲያቢሎስም ካነቀው ስህተት አይርቁም እኛ ግን በእግዚአብሔር ታቦተ ህግ በፅዮን ውስጥ እንስግድ ዘንድ ይገባል፡፡ መጀመሪያዋም እሷ ናት ዛሬም አሁንም እሷ ናት ምሳሌዋም ፍሬዋም የመድሃኒታችን እናት ማርያም ናት፡፡ እንስግድላት ዘንድ የእግዚአብሔር ታቦተ ህግ በእሷ ስም ተባርካለች፡፡" ክብረ ነገሥት
የበዓሉ ምክንያት፡-
ታቦተ ጽዮን በአምስቱ የፍልስጤም ከተሞች ተዓምራቷን ገልጻ 20 ዓመታት በኋላ በድል አድራጊነት ወደ እስራኤል የገባችበት፡፡ 1ኛሳሙ ምዕ5- 6
 ታቦተ ጽዮን የፍልስጤማዊያንን ጣኦት ዳጎንን ያፈራረሰችበት፡፡ 1ኛሳሙ ምዕ5
 ኢትዮጵያዊቷ ንግሥተ አዜብ ሳባ ወደ ፍልስጤም በመሄድ የሰሎምንን ጥበብ ማድነቋና በልጇ በእምነ መለክ (ቀዳማዊ ምኒልክ) አማካኝነት ከሌዋዉያን ካህናት ጋር በመሆን ታቦተ ጽዮን ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የገባችበት፤ 1ኛነገ 10 1-13 2ኛዜና መዋዕል 91-12
 ስለ ታቦት ክብር በስፋት የሚገለጥበት
 በሀገራችን በአክሱም የመጀመሪዋ ቤተክርስቲያን አክሱም ጽዮን የታነጸችበት በዓል ነው፡፡
የቃል ኪዳን ታቦት ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን ክፍል አንድ
የአምላክ ማደሪያ ቅድስት ድንግል ማርያም በልዑል እግዚአብሔር ትእዛዝ ጥበብና ማስተዋል በተሰጠው በባስልኤል እጅ በተሰራችው የቃል ኪዳን ታቦት ትምስላለች ይኽቺ
የእግዚአብሔር የጌትነቱ መግለጫ የኾነችው
በፍልስጥኤም ይምለክ የነበረ ጣዖትን ቀጥቅጣ ያጠፋች፤
በድፍረት ሊነካት የሞከረ ኦዛን የቀሰፈች፤
በታላቅ ክብር ወደ ሀገሯ ስትመለስ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት በታላቀ መንፈሳዊ ደስታ በፊቷ የዘመረላት
ልጁ ሰሎሞንም ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርቶ በክብር ያኖራት ናት፡፡

አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ

    የከበረ ገድለኛ አባት የዋልድባው አባ ሳሙኤል የአባቱ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም ደግሞ ዓመተ ማርያም ነው። እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጋግ ናቸው፤ እነርሱም በአክሱም ሀገር ሲኖሩ ሁለት ልጆችን ወለዱ። አንደኛው ስሙ...

በብዙ አንባቢያን የተነበቡ