ሀልወተ እግዚአብሔር

ሀልወተ እግዚአብሔር ለእግዚአብሔር ህላዌ ማስረጃነት ከሚቀርቡት በርካታ ጉዳዮች መካከል በተለይ የፍጥረታት ሥነ ሥርዓትና አሠራሩ፣ የህሊና ምስክርነት ፣የሠው ልጆች የተፈጥሮ ዝንባሌ፣ የቃለ እግዚአብሄር፣ የታሪክ ምስክርነት ወዘተ….. ይገኙበታል፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ ወፎችንና እንስሳትን ብትጠይቋቸው ብዙ ሊያስተምሯችሁ በቻሉ ነበር፡፡ በምድር ላይ እና በባህር ውስጥ የሚኖሩትን ፍጥረቶች ጥበብ እንዲያስተምሯችሁ ብትጠይቋቸው ሁሉም እግዚአብሔር አንደሰራቸው ያስረዱአችኋል፡፡ የፍጥረቶቹን ሕይወት የሚመራ እግዚአብሔር ነው፡፡ የእያንዳንዱ ሰው ነፍስ በእግዚአብሔር ሥልጣን ስር ነው፡፡›› (መ.ኢዮ 12÷7-10) በማለት ዓለምን ያስገኘ እግዚአብሔር መሆኑን በግልጽ ያስተምራል፡፡ መዝሙረኛው ቅ/ዳዊትም ይህንን ሀሳብ ሲያጠናክረው ‹‹ሰማያት የእግዚአብሔር ክብር ይናገራሉ፣ የሰማይ ጠፈሮችም የእግዚአብሔር ሥራ ያውጃሉ፡፡›› (መዝ19፡1) በማት ከእግዚአብሔር ውጭ ይህች ዓለም ሌላ አዛዥና ባለቤት እንደሌላት ምስክርነቱን አስቀምጧል፡፡ በአንድ ወቅት በአቴና ከተማ የሚኖሩ ሰዎች ስለ እግዚአብሄር ሀልወት ለማመንና ለመቀበል ተቸግረው መስዋዕት እያቀረቡ መስዋዕት የሚያቀርቡለትን አምላክ ባለማወቃቸው ‹‹ ለማይታወቅ አምላክ›› ብለው ጽፈው ሲያመልኩ ግን የሚያመልኩትን አምላክ ሳያውቁ እንደነበረ ሀዋርያው ቅ/ጳውሎስ አርዮስፋጐስ በተባለው ሥፍራ ቆሞ የክርስትናን ሃይማኖት እንዴት እንደሰበካቸውና የማይታወቀውን አምላክ ሲገልጽ ‹‹ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሠማይና የምድር ጌታ ነውና….›› (የሐዋ 17፡24) በማለት ስለእግዚአብሔር ሀልወት ለአቴና ሰዎች ገልጧል፡፡

አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ

    የከበረ ገድለኛ አባት የዋልድባው አባ ሳሙኤል የአባቱ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም ደግሞ ዓመተ ማርያም ነው። እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጋግ ናቸው፤ እነርሱም በአክሱም ሀገር ሲኖሩ ሁለት ልጆችን ወለዱ። አንደኛው ስሙ...

በብዙ አንባቢያን የተነበቡ