አምስቱ አዕማደ ምስጢራት
፩. ምስጢረ ሥላሴ
፪. ምስጢረ ሥጋዌ
፫. ምሥጢረ ጥምቀት
፬. ምስጢረ ቁርባን
፭. ምስጢረ ትንሳኤ ሙታን
፪. ምስጢረ ሥጋዌ
፫. ምሥጢረ ጥምቀት
፬. ምስጢረ ቁርባን
፭. ምስጢረ ትንሳኤ ሙታን
‹‹አምድ›› ማለት ‹‹ምሶሶ›› ማለት ሲሆን ‹‹አዕማድ››ማለት ደግሞ ምሶሶዎች ማለት ነው፡፡
አዕማደ ምስጢር ማለት ደግሞ ‹‹የምስጢር ምሶሶዎች ማለት›› ነው፡፡
እነዚህ ምስጢራት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መሠረታዊ የሆኑ የሃይማኖት አስተምህሮዎች
የሚገለጡባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ምስጢር ለምን ተባሉ ስንል በጣም ረቂቅና የሰው ልጆች ሕሊና መርምሮ ሙሉ ለሙሉ ለመረዳት ከባድ ስለሆኑነው፡፡ እነዚህ ምስጢራት ለክርስቲኖች ብቻ የሚነገሩ በመሆናቸው ነው፡፡
የአዕማደ ምስጢር ምንጭና ስያሜ መሰረቱ ምንድን ነው?
አዕማደ ምስጢራት ይዘት ምንጭ የጌታና የሐዋርያት ትምህርት ነው፡፡
ይሁን እንጅ አነሳሱ በጸሎተ ሃይማኖት ወይም አባቶቻችን ምዕመናንን በትክክለኛው ሃይማኖት ለማጽናትና መናፍቃንን ድል ለመንሳት በተካሄዱ በጉባዔ ኒቂያና ቁስጥንጥንያ ነው፡፡
ከዚህ በኋላ አባቶቻችን ጸሎተ ሃይማኖትን መሰረት በማድረግ ከብሉያት ከሐዲሳትና ከሊቃውንት መጽሃፍት በማውጣጣት አምስቱ አዕማደ ምሥጢራትን አዘጋጅተዋል፡፡
፩. ምስጢረ ሥላሴ
‹‹ሥላሴ››የሚለው ቃል ‹‹ሠለሰ ሦስት አደረገ ››
ካለው የግዕዝ ግዝ የተገኘ ሲሆን ሦስትነት ማለት
ነው፡፡
ይህ ምስጢር የእግዚአብሔርን አንድነት ሦስትነት
የምንማርበት የትምህርት ክፍል ነው፡፡ይህም ልዩ ሦስትነት ይባላል፡፡
ይህም እግዚአብሔር አንድ አምላክ በሦሰት አካል/ኩነታት ወይም ሁኔታዎች/ለአበው፣ ለነቢያት
ለሐዋርያት የተገለጠውን መሰረትበማደረግ ነው፡፡
በአጭር ቃል በባህርይ፣በፈቃድና በስልጣን አንድ
የሆነውን እግዚአብሔር፣የአካል፣የስምና የግብር
ሦስትነት እንዳለው የምናምነው እምነት
ምሥጢር ሥላሴ ይባላል፡፡
፩.፩. የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት
፩.፩.፩.የሥላሴ ሦስትነት
የሥላሴ ሦስትነት በአካል፣በስምና በግብር ነው፡፡
፩.፩.፩.፩.የስም ሦስትነት
እነዚህ ሦስት አካላት የየራሳቸው ልዩ ስም አላቸው፡፡
አብ፣ወልድ፣መንፈስ ቅዱስ ይባላሉ፡፡አንዳቸው በሌላው ስም አይጠሩም፡፡ይህ ስማቸው ግን ግብራቸውን የሚገልጥ ነው፡፡
‹‹ ሂዱና አህዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዝሙራቴ አድርጓቸው››ማቴ፳፰፤፲፱
፩.፩.፩.፩.የግብር ሦስትነት
በግብር አብ ወላዲና አስራጺ፣ወይም መገኛ ነው፡፡ ወልድ ተወላዲ/ከአብ የተገኘ/ መንፈስ ቅዱስም ሠራጺ/ከአብ የወጣ/ ነው፡፡
ወልድ ከአብ ተወለደ ስንል እምቅድመ ዓለም ነው፡፡
ወልድ ስለ ራሱ ሲናገር ‹‹ ምድርም ከመፈጠሯ አስቀድሞ፣ቀላያትም ገና ሳይፈጠሩ፣እኔ ተወለድኩ፣ተራሮች ገናሳይመሰረቱ፣ከኮረብቶች በፊት እኔ ተወለድኩ፡፡››ምሳ፰፤፳፫-፳፭
አብ ስለ ባህርይ ልጁ ሲናገር ‹‹ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፡፡›› ማቴ፫፤፲፯
መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹ እኔም አይቸዋለሁ እርሱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ እመሰክራለሁ፡፡››ዮሐ፩፤፴፬
ሦስት መቶ አስራ ስምንቱ ሊቃውንትም በሃይማኖተ አበው
*‹‹ሁሉን የፈጠረ ፣ሰማይና ምድርን ፣የሚጣየውንና የማይታየውን በፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን፣እምቅድመ አለም ከአብ በተወለደው ከዓለም በፊት ከአብ ህልው ሆኖ የኖረው፣
የአብ አንድ ልጅ በሆነው በአንድጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናምናለን….ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከባህርይ አምላክ የተገኘ የባህርይ አምላክ ነው የተወለደ እንጅ ያልተፈጠረ››ሃይማኖተ አበው
*‹‹ አብ ብርሃን ነው፤ከአብ የተወለደ ቃሉ ወልድም ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው፤ከአብ የሰጠረጸው መንፈስ ቅዱስም ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው፤
ከአብ የወልድ መወለድ .የመንፈስ ቅዱስ መሥረጽ እጅግ ይደንቃል እንጂ አይነገርም ››
ቅዱስ ዲዮናስዮስ
መንፈስ ቅዱስ ከአብ ሰረጸ ስልን እምቅድመ ዓለም ነው፡፡
*‹‹እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ/ጰራቅሊጦስ/ እርሱም ከአብ የሚወጣ/የሚሰርጽ/ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ስለእኔ ይመሰክራል፡፡››ዮሐ፩፭፤፳፮፤፳፯
ሦስት መቶ አስራ ስምንቱ ሊቃውንትም በሃይማኖተ አበው ‹‹ ጌታና ማሕያዊ በሆነው፣ከአብ በሠረፀው በመንፈስ ቅዱስእናምናለን፡፡ከአብና ከወልድም ጋር በአንድነት እንሰግድለታለን፤እናመሰግነዋለንም››
ከላይ ቀረበው መንገድ የሦስቱም የየራሳቸው ግብር ወይም ሥራ ይኑራቸው እንጅ ፤ቅዱስ አትናቴዎስ እንደተናገረው
‹‹ አብ አምላክ ነው፣ወልድም አምላክ ነው፤መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው፣ነገር ግን ሦስት አማልክት አይባሉም ፤አንድአምላክ ነው እንጅ›› ቅዱስ አትናቴዎስ
‹‹ወልድ ከአብ ተወለደ፣መንፈስ ቅዱስም ከአብ ሠረጸ ማለት የፀሃይ ብርሃንና ሙቀት ሁለቱም ከክበቡ ባለመቀዳደም አንድጊዜ ተገኙ እንደማለት ያለ እንጅ እንደ ሥጋ ልደት ሕገ ሰብዕን አይከተልም ፡፡
ስለዚህ በሥጋ ልደት አባት ልጁን እንደ ሚቀድመውና እንደ ሚበልጠው አብ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ አይበልጥም፣እነርሱም ከአብ አያንሱም፡፡በሥላሴ ዘንድ መቀዳደምም መበላለጥም የለም፡፡
፩.፩.፩.፫.የአካል ሦስትነት
የአካል ሦስትነት ማለት ሦስቱ አካላት እያንዳንዳቸው ፍጹም አካል፣ፍጹም ገጽ፣ፍጹም መልክ አላቸው ማለት፡፡
ይህ አካል ተጨባጭ ወይም ቁሳዊ አካል አካል አይደለም፡፡መንፈሳዊ አካል ነው፡፡ምሳሌ፤-ነፋስ ምንም ዝርው ቢሆንምአካላዊ ነው፣ልንጨብጠውና ልንዳስሰው፣ልናየውም ግን አንችልም ፡፡ባለ መታየቱ ግን የለም ልንለው አንችልም ፡፡ባህርሲያናውጽ፣ዛፍ ሲወዛውዝ ግን በሥራው መኖሩን እናያለን፡፡
ከነፋስ የሰው ነፍስ ተረቃለች፣ከሰው ነፍስ የመላዕክት ተረቃለች፣ከመላዕክት ደግሞ የሁሉ ፈጣሪ እግዚብሔር በማይነገርመጠን ረቀቅ ነው፡፡ይህ ረቂቅ አካል የሌለበት ቦታ የለም፡፡
የሥላሴ አካል ግን እንደ ነፋስ ዝርው አይደለም፡፡
ሦስቱ አካላት አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በባህርይ፣በህልውና በመለኮት አንድ ናቸው፡፡
በባህርይ አንድ ናቸው ስንል ሦስቱ አካላት በዘላለማዊነት ፣ሁሉን ቻይነት፣ ምልዕነት፣ረቂቅነትና በመሳሰሉት ነው፡፡
በህልውና ማለት በአኗኗር ማለት ነው፡፡
፩.፩.፪.የሥላሴ አንድነት
በመለኮት፣በአገዛዝ፣በሥልጣን፣ይህንን ዓለም ፈጥሮ በማሳለፍ፣በፈቃድ እና በመሳሰሉት ነገሮች አንድ ናቸው፡፡
በህልውና አንድ ናቸው ስንል አንዳቸው በአንዳቸው ውስጥ ይኖራሉ ማለት ነው፡፡
አብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ህልው ነው፡፡/ይኖራል/፣
ወልድም በአብና በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ ህልው ነው፣
መንፈስ ቅዱስም በአብና በወልድ ውስጥ ህልው ነው፡፡... ሃይማኖት3

No comments:
Post a Comment