ሃይማኖት 1


ሃይማኖት ሃይመነ አሳመነ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም በአንድ አምላክ ማመን እና ለአንድ አምላክ መታመን ማለትን ያመለክታል ::

  በዓይናችን ለምናየው ለግዙፉ ዓለምና ለማይታየው ለረቂቁ ዓለም ፈጠሪ አስገኝ መጋቢአለው እሱም እግዚአብሔር ነው ብሎ ማመን የሃይማኖት የመጀመሪያ ክፍል ነው

    እምነት ማለትም አምነ አመ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሆኖ ትርጉሙ ለእግዚአብሔር መታመንነና በእግዚአብሔር ማመንን ይገልጣ ነው ቅዱስ ዻውሎስዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደተፈጠሩ የሚታየውም ከማይታየው እንደሆነ እናውቃለንዕብ 11 3  በማለት እንደተናገረ የሰው ልጅ የሃይማኖት ትምሕርት ከመማሩ አስቀድሞ በህሊናው በመመራት የእግዚአብሔርን መኖር ማመን ተገቢ ነው

  የሃይማኖት ትምሕርት የሚነገረው የእግዚአብሔር ቃል እውነት መሆኑን በመቀበል የምናምነው የምንማርበት እንጅ እንደ ዓለማዊ የሳይንስ ዕውቀት የተማርነው ሁሉ በዘመናዊ መሳሪያ አረጋግጠን የምንደርስበት አይደለም ሃይማኖት ቁስ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ታምነው የሚኖሩት ሕይወት ነውና የእግዚአብሔር መንግሥት ተቃዋሚዎች አጋንንት ሳይቀሩ አይጠቀሙበትም እንጅ የአምላክን መኖር ያምናሉ ይንቀጠቀጣሉም ያዕ 2 19

    በዚህ ዓለም በራሱ የተገኘ ምንምነገር እንደሌለና ለሁሉም አስገኝ ፈጣሪ እንዳለው ይታወቃል የሳይንሱ የምርምር ውጤት፡ ሁሉን የፈጠረው ኃይል በሥጋዊ ጥበብ ተመራምሮ አልደረሰበትም በሃይማኖት ትምሕርት ግን ሁሉን ያስገኘ እግዚአብሔ መሆኑን መረዳት ይቻላል የሰው ልጅ የሠራቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚያንቀሳቅስ ባለሞያ እንደሚያስፈልጋቸው ሁሉ ይህን ዓለምም የሚያንቀሳቅሰውና የሚመራው አስገኝው (የፈጠረው) አምላክ ብቻ ነውና ሰው ይህን የአምላክ ሥራ አይቶ ፈጣሪውን ማመስገን ሲገባውየተፈጥሮ ክስተት ነውሲል ይደመጣል

       ለምሳሌ ጨለማና ብርሃንን ወቅቶችንና ዘመናትን የሚያፈራርቅ የሰውን ልደትና ሞት የሚወስን ሌሎችም ፍጥረታት ሥርዓታቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ የሚያደርግ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠራቸው አምላክ ብቻ ነው የሰው ልጅ የተደረጉና ያለፉ ታሪኮችን ከመመዝገብ ያለፈ ችሎታና አቅም  የለውም

  እምነት ቅዱስ ዻውሎስበሥጋ ዓይን የማናየውንና ተስፋ የምናደርገውን የሚያስረዳና የሚያስረግጥ መሳሪያ ነው ዕብ 11 1 በማለት እንዳስተማረ በሃይማኖት የሚኖር ሰው ዕለት ዕለት በሚያደርግለት የቸርነት ሥራው አምላኩን ያየዋል ለማያምንና ፍረጥረታዊ ለሆነ ሰው ግን የሃይማኖት ነገር ለእሱ ሞኝነት ስለሆነ ለህሊናው ሊረዳውና  ሊቀበለው  ይችልም 1ቆሮ 2 9 3

   ሃይማኖት ሰዎችና እግዚአብሔር የሚገናኙባት መንታነት የሌለባት አንዲት መንገድ ናት ኤፌ 4 4 በዓለማችን የሚገኙት የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት የግል ጥቅምና የሥልጣን ሱስ የተጠናወታቸው ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ ለራሳቸው ክብርና ዝና ቅድሚያ የሚሰጡ አዲስ ነገር በመሥራት ታዋቂነትን ለማትረፍ የሚፈልጉ ግለሰቦች የመሠረቷቸው ድርጅቶች መሆናቸው ግልጽ ነው ምክንያቱም ሁሉም እየተለዩ የወጡት ከመጀመሪያዋ አንዲት ሃይማኖት ነውና ::

    ሃይማኖት ከቅዱሳን መላእክት ጀምሮ ፀንቶ የሚኖር የአምላክና የፍጡራን ግንኙነት ነው።ለምሳሌ ቅዱሳን መላእክት ሰይጣን ፡ዲያብሎስፈጣሪ ነኝባለበት ወቅት ቅዱስ ገብርኤልአምላካችን እስኪገለጥልን ድረስ በእምነታችን እንጽናብሎ የተናገረውን ቃል መሪ በማድረግ በሃይማኖት ጸንተው ተገኝተዋል ራዮሐ 12 7

ከአዳም እስከ ሙሴ የነበሩ ቅዱሳን ሰዎች የተጻፈ ህግ ሳይኖራቸው በህገ ልቡና እየተመሩ በሃይማኖት ጸንተው ኖረዋል

  ከሙሴ እስከ ክርስቶስ የነበሩ ቅዱሳን ሰዎች ቃሉን ሰምተው በመጠበቅ በሃይማኖታቸው ተመስክሮላቸው አልፈዋል ።ሐዋርያት ቃሉን ሰምተው ተአምራቱን አይተው ሀብተ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ሃይማኖታቸውን ጠብቀው ለሌላውም አስተምረው ክርስትናን በዓለም አስፋፍተው በክብር አልፈዋል

    ከሐዋርያት በኋላ የተነሱና እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚቀጥሉ ክርስቲያኖች ከቅዱሳን ሕይወትና ከመጻህፍት ተረድተው ከመምህራን እየተማሩ በየዘመናቱ የሚደረገውን ተአምራት እያዩ በሃይማኖት ጸንተው ኖረዋል ይኖራሉም ስለዚህም ሃይማኖት በአምላክ ፈቃድ የሆነና በዘመናት ሁሉ የነበረ ያለና የሚኖር ሕይወት ነው  

     ከዚህ ከተቀደሰና ከትትክለኛው መንገድ የወጡ ሰዎች ከመጠራጠር ተነስተው እኛ ትንንሽ ከርስቶሶች ነን እስከ ማለት ደርሰዋል ሰው ለህሊናው ገደብ ካላበጀለትና ለእግዚአብሔር ክብር መስጠትን ከረሳ መጨረሻው ጥፋት መሆኑን እንረዳለን

  ሃይማኖት በዘመናት ብዛት የማታረጅ የማትታደስ በየዘመኑ በሚነሳ ሥልጣኔ የማትለወጥ ሁሌም አዲስ ናት ሃይማኖት በልብ አምኖ በአንደበት መስክሮ የሚዳንበት ህይወት ነው ሮሜ 10 10 ሃይማኖታችን በምግባር የሚገለጥ መሆን አለበት በሥራ የማይገለጥ ሃይማኖት ነፍስ የተለየችው ሥጋበድንማለት ነውና ።...


No comments:

Post a Comment

አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ

    የከበረ ገድለኛ አባት የዋልድባው አባ ሳሙኤል የአባቱ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም ደግሞ ዓመተ ማርያም ነው። እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጋግ ናቸው፤ እነርሱም በአክሱም ሀገር ሲኖሩ ሁለት ልጆችን ወለዱ። አንደኛው ስሙ...

በብዙ አንባቢያን የተነበቡ